News and Events
ድርጅቱ ለ10 የፋብሪካ ሠራተኛ ማኅበራት ከ6 መቶ ሺህ ብር በላይ ግምት ያለው የዓይነት ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ፡፡ 2025-12-28 13:10:43 |
| ደብረ ብርሃን፣ኅዳር19/2018(ደብመኮ)፡-ዕድገት ኢትዮጵያ ለአፍሪካ የልማት ድርጅት ለ10 የፋብሪካ ሠራተኛ ማኅበራት ከ6 መቶ ሺህ ብር በላይ ግምት ያለው የቢሮ ቁሳቁሶች ድጋፍ አድርጓል፡፡የድርጅቱ ፕሮግራም ስራ አስኪያጅ አቶ ጥበቡ እለፋቸው እንደገለጹት በደብረ ብርሃን ከተማ ከሚገኙ ከተመረጡ 10 ግዙፍ ፋብሪካ ሠራተኛ ማህበራትና ከኢንዱስትሪ ፓርክ ጋር እየሰሩ እንደሚገኙ አስረድተዋል፡፡ ፕሮጀክታቸው በዋናነት የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት መልካም እንዲኾን፣የሰራተኞች ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር፣መብትና ጥቅማቸው እንዲከበር የአቅም ግንባታ ስልጠና በመስጠት የተጠናከረ የሰራተኛ ማኅበር እንዲፈጠር እየሰራን ነው ብለዋል፡፡ ዛሬም ለ10 የፋብሪካ ሠራተኛ ማኅበራት ከ6 መቶ ሺህ ብር በላይ ወጪ የኾነባቸው የቢሮ ጠረጴዛ፣ወንበር፣መደርደሪያ እና የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያዎችና ፋይል ማቀፊያዎችን ድጋፍ ማድረጋቸውን አስታውቀዋል፡፡ የደብረ ብርሃን ከተማ ስራ ስልጠና መምሪያ ባለሙያ መስታወት እንዳለ በበኩላቸው ዕድገት ኢትዮጵያ ለአፍሪካ የልማት ድርጅት ከዚህ በፊት ለፋብሪካ ሰራተኞች የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን መስጠቱንና የልምድ ልውውጥ ፕሮግራሞችን ማመቻቸቱን አስታውሰዋል፡፡ በዚህም የኢንዱስትሪ ሰላም ይፈጠራል፣በአሰሪና ሰራተኛ መካከል ጤናማ ግንኙነት ይኖራል፣ምርታማነት ያድጋል በውጤቱም የጋራ ተጠቃሚነትን በመጨመር ፋይዳው የጎላ ነው ብለዋል፡፡ ድርጅቱ የኢንዱስትሪ ሰላም እንዲፈጠር ከሚያደርገው ስራ በተጨማሪ የፋብሪካ ሰራተኛ ማኅበራት እንዲጠናከሩ በዕለቱም ለ10 ማኅበራት የቢሮ መገልገያ ግብዓቶች ድጋፍ ማድረጉን አመልክተዋል፡፡ ከደብረ ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ሰራተኛ ማኅበር የመጡት አቶ ጌታቸው ወርቁ አክለው እንደገለጹት ከድርጅቱ የተሰጣቸው የቢሮ መገልገያ ቁሳቁሶች ከዚህ በፊት የነበረባቸውን ችግር የሚያቃልል ነው ብለዋል፡፡ ዛሬ ከተደረገላቸው ድጋፍ በተጨማሪም የተለያዩ ስልጠናዎችን በመስጠት የሰራተኛውን አቅም በማጎልበት ሰላማዊ የአሰሪ ሰራተኛ ግንኙነት እንዲፈጠር ከጎናቸው ኾኖ እየደገፋቸው በመኾኑ አመስግነዋል፡፡ |
![]() ![]() ![]() ![]() ![]() ![]() ![]() ![]() ![]() |









